Kebena Logo

የቀቤና ልዩ ወረዳ የመንግስት
ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ፅህፈት ቤት

የቀቤና ልዩ ወረዳ – ማህበራዊ ዘርፍ

በማህበራዊ ዘርፍ የተለያዩ ክፍሎች በተግባር እድገት ለማምጣት የህዝብ ተፈጥሯዊ ፍላጎቶችን ይወክላሉ።

ሴቶችና ህፃናት ጉዳዮች ጽ/ቤት

የሴቶችን በልማት፣ በመልካም አስተዳደርና በዲሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ እኩል ተሳትፎና ተጠቃሚነትን ማረጋገጥ፤ የህፃናትን መብትና ደህንነት ማስጠበቅና የፆታ ዕኩልነትን ማስፈን፡፡

የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት

በልዩ ወረዳዊ በክልላዊና በሀገራዊ ጉዳዮች ላይ የህብረተሰቡን ሁለንተናዊ ተሳትፎ የሚያነሳሳ፣ የሚያጎለብትና ተጠቃሚ የሚያደርግ የኮሚዩኒኬሽን ስርአትና የህዝብ ግንኙነት ስራዎችን በማጎልበት ተአማኒና ጥራቱን የጠበቀ መረጃ በማድረስ፤ የሚዲያ ሞኒተሪንግና የህዝብ አመለካከት ጥናት ስራዎችን በማከናወን እንዲሁም የመንግስት መረጃ ማዕከልና ዲጂታል ሚዲያዎችን በማልማት በመረጃ የበለጸገ ህብረተሰብ መፍጠር እና የልዩ ወረዳው ገጽታ መገንባት ነው፡፡

ጤና ጽ/ቤት

ሁሉን አቀፍ የጤና አገልግሎት የጤና ሽፋን ላይ በማተኮር፤ ህብረተሰቡን ከድንገተኛ አደጋ በመጠበቅ፤ ወረዳ ትራንስፎርሜሽን በመተግብር እና የጤና ሥርዓትን ምላሽ ሰጭነት በማረጋገጥ “የህብረተሰቡን የጤና ሁኔታ ማሻሻል” ነው፡፡

ትምህርት ጽ/ቤት

ከቅድመ አንደኛ ደረጃ እስከ መካከለኛ ደረጃ የግዴታ ትምህርት ፤ ሁለተኛ ደረጃን የነፃ ትምህርት በሳይንስና ተስማሚ ቴክኖሎጂ የተደገፈና በብቁ አመራር የሚመራ ትምህርት በመስጠት ለሁሉም በፍትሀዊነት ጥራት ያለው ትምህርት በማዳረስ የዜጎችን አዕምሮአዊ፣ አካላዊ፣ ማህበራዊ፣ ስሜታዊ እንዲሁም መልካም እሴቶችን በማጐልበት ለሀገራችን ነባራዊ ሁኔታዎች ምላሽ የሚሰጡና የሃገሪቱን የዕድገት ጉዞ ማሳካት የሚችሉና በአለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ የሆኑ ብቁ ዜጐችን ማፍራት ነው፡

ሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳዮች ጽ/ቤት

በልዩ ወረዳ በልዩ ልዩ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ችግሮች ምክንያት በድህነት፣ተጋላጭናመገለል ውስጥ ለሚገኙ ዜጐች የተለያዩ ድጋፎች እንዲያገኙ ማድረግ የሥራ ስምሪት አገልግሎት እንዲስፋፋ፣ የኢንዱስትሪ ሠላም እንዲሰፍን፡ የሠራተኛውን ጤንነትና ደህንነት እንዲጠበቅ፣ የሥራ አከባቢዎችን እንዲሻሻልና የዜጐችን ማህበራዊ ጥበቃ አገልግሎት የአካል ጉዳተኞች እኩል እድልና ሙሉ ተሳታፊነት እንዲረጋገጥ፣ አረጋውያን ድጋፍና እንክብካቤ እንዲያገኙና ተሳትፎአቸው እንዲጐለብት ማድረግ

ወጣቶችና ስፖርት ጽ/ቤት

የልዩ ወረዳችን ወጣቶች ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊና ፖለቲካዊ ተሳትፎና ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ምቹ ሁኔታ በመፍጠርና ህዝባዊ መሰረት ያለውን ስፖርት በማስፋፋት የዜጎችን አካላዊና አእምሮአዊ ብቃት በመገንባት የልዩ ወረዳና የክልልን ብልፅግና ማረጋገጥ

ባህልና ቱሪዝም ጽ/ቤት

የልዩ ወረዳችን ቋንቋ በማጥናት፣በመጠበቅ፣በማልማት እና በማስተዋወቅ የአገልግሎት አሰጣጥን በማዘመን የወረዳችን ሕዝብ ባህል፣ታሪክ፣ቋንቋ፣ስነ-ጥበብ፣ዕደ-ጥበብ እና ፎክሎር እንዲጠና፣ እንዲጠበቅ፣ በዘላቂነት እንዲለማ እና የአገልግሎት አሰጣጡን ጥራት እና ብቃት ያለው በማድረግ  እንዲሁም የዕደ-ጥበብ ምርቶቻችንን ለገበያ በማስተዋወቅ መልካም ገጽታ ተፈጥሮ ሴክተሩ ለልዩ ወረዳችን የሚያበረክተውን ልማታዊ አስተዋጽኦ ማሳደግ እና  የህብረተሰባችንን ተጠቃሚነት በማረጋገጥ የመሪነት ሚና በመጫወት በመንግስት እና በህዝባችን መካከል ቀልጣፋ እና ዉጤታማ የሆነ የአገልግሎት ፍሰት እንዲኖር በማድረግ በዋና ዋና የልዩ ወረዳዉ፣የከልላዊ እና ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ንቁ ተሳትፎ በማድረግ ብሄራዊ መግባባትን በመፍጠር  የሀገራችንን ሰላም፣ ልማ ት እና ብልፅግናን ማረጋገጥ  ነው፡፡

ሳይንስና ቴክኖሎጂ ጽ/ቤት

ለልዩ ወረዳው ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ልማት ጉልህ አስተዋፅኦ የሚያደርጉ የሳይንስና የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ስራዎችን ለህብረተሰቡ በአግባቡ በማልማት፣ በመተግበርና በማስፋት ወረዳዊ ብሎም ክልላዊ የተወዳዳሪነት አቅምና በቴክኖሎጂ የዳበረ የአሰራር ስርዓት መፍጠር ነዉ፡፡

ማህበራዊ እድገት ለማምጣት አብረን እንስራ

የማህበረሰባችንን ፍላጎት በማሟላት ዘላቂ እድገት እናምጣ

አግኙን

የማህበራዊ ዘርፍ ዜናዎች

ማህበራዊ

በልዩ ወረዳው የጤና ቡድን የወጣቶች አደረጃጀት ፐብሊክ ሰርቫንትን 2 ለ 0 በሆነ ውጤት አሸነፈ።

በልዩ ወረዳው የጤና ቡድን የወጣቶች አደረጃጀት ፐብሊክ ሰርቫንትን 2 ለ 0 በሆነ ውጤት አሸነፈ...

ተጨማሪ ያንብቡ
ማህበራዊ

በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ዲስትሪክት በቀቤና ልዩ ወረዳ በጫንጮ ውጥኝ ት/ቤት ለተማሪዎች የመማሪያ ደብተር ድጋፍ አደረገ ። ወልቂጤ፣ ኅዳር 4/2018 ዓ.ም በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ዲስትሪክት በቀቤና ልዩ ወረዳ በጫንጮ ውጥኝ ት/ቤት ለተማሪዎች የመማሪያ ደብተር ድጋፍ አደረገዋል ።

በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ዲስትሪክት በቀቤና ልዩ �...

ተጨማሪ ያንብቡ
ማህበራዊ

በወቅታዊ የጤና ጉዳይ የተሰጠ መግለጫ

በወቅታዊ የጤና ጉዳይ የተሰጠ መግለጫ...

ተጨማሪ ያንብቡ
ማህበራዊ

የሴቶች የልማት ህብረት አደረጃጀት ለሁለንተናዊ ብልፅግና መሠረት መሆኑ ተገለፀ ።

የሴቶች የልማት ህብረት አደረጃጀት ለሁለንተናዊ ብልፅግና መሠረት መሆኑ ተገለፀ ። (ወልቂ�...

ተጨማሪ ያንብቡ
ማህበራዊ

የሴቶችን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ የተጀመረው ጥረት ተጠናክሮ መቀጠል ያለበት ነው :-ወ/ሮ ፈቲያ ሱልጣን

የሴቶችን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ የተጀመረው ጥረት ተጠናክሮ መቀጠል ያለበት ነ...

ተጨማሪ ያንብቡ
ማህበራዊ

የቀቤና ልዩ ወረዳ የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ዌብሳይት በማልማት የማስተዋወቂያ መድረክ አካሂዷል ።

የቀቤና ልዩ ወረዳ የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ዌብሳይት በማልማት የማስተዋወቂ�...

ተጨማሪ ያንብቡ
ማህበራዊ

የወባ በሽታ መከላከል ቅድመ ማስጠንቀቂያ!

የክረምቱ ወቅት አልፎ የበጋው ወቅት መተካቱን ተከትሎ በሚፈጠር ሙቀትና ውሃ በሚያቁሩ ኩሬዎ�...

ተጨማሪ ያንብቡ
ማህበራዊ

በቀቤና ልዩ ወረዳ መደበኛ ክትባት ሳይከተቡ ላመለጣቸው ህፃናት የክትባት ዘመቻ በሩሙጋ ቀበሌ ተጀምሯል ።

በቀቤና ልዩ ወረዳ መደበኛ ክትባት ሳይከተቡ ላመለጣቸው ህፃናት የክትባት ዘመቻ በሩሙጋ ቀበ�...

ተጨማሪ ያንብቡ