Kebena Logo

የቀቤና ልዩ ወረዳ የመንግስት
ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ፅህፈት ቤት

የቀቤና ልዩ ወረዳ – ኢኮኖሚ ዘርፍ

የቀቤና ልዩ ወረዳ ኢኮኖሚ ዘርፍ በብዙ ክፍሎች ተከፍሎ በወረዳው የኢኮኖሚ እድገት እንዲያገለግል ይሰራል።

ገቢዎች ጽ/ቤት

መንግስት ከህብረተሰቡ የተጣለበትን የመልማት ፍላጎት በብቃት መወጣት እንዲችል የሚያስፈልገውን በጀት ለመሸፈን ያስችለው ዘንድ መ/ቤታችን ኢኮኖሚው ከሚያመነጨው ሀብት ገቢ የመሰብሰብ ሙሉ የሥልጣን ውክልና ወስዶ እየሰራ ይገኛል፡፡ በዚህም መሠረት መ/ቤቱ ከህዝብና መንግስት የተሰጠውን ተልዕኮ ለመወጣት የሚያስችለውን የተለጠጡ ስትራቴጂክ ግቦችን በመጣል እና በመተግበር ባደረገው ሰፊ እንቅስቃሴ የገቢ አሰባሰብና አስተዳደር ሥራዎችን ቀልጣፋና ውጤታማ ለማድረግ የሚያስችሉ የታክስ ማሻሻያ ፕሮግራሞች እንዲሁም የገቢ ተልዕኮ ፈጻሚ ግንባታ ሥራዎች በስፋት የተተገበሩ በመሆናቸው የገቢ አሰባሰብ አፈጻጸሙ አበረታች እድገት አሳይቷል፡፡

ፋይናንስ

የልዩ ወረዳው ፋይናንስ ጽ/ቤቱ በአዋጅ በተሰጠው ስልጣንና ተግባር መሠረት የልዩ ወረዳውን መንግስት በጀት ማዘጋጀትና ማስተዳደር፣ በተፈቀደው በጀት መሠረት ክፍያ መፈጸም፣ የበጀቱን አፈጻጸም መከታተል፣ መገምገምና መቆጣጠር፤ የልዩ ወረዳውን መንግስት የበጀት፣ የሂሳብ፣ የክፍያና ጥሬ ገንዘብ እና የውስጥ ኦዲት ሥርዓት መዘርጋትና በስራ ላይ እንዲውል ማድረግ፣ የልዩ ወረዳውን መንግስት የገንዘብ ሰነዶች፣ ገንዘብና ንብረቶች መያዝና ማስተዳደር፣የልዩ ወረዳውን መንግስት የብድርና እርዳታ ስምምነቶችን መፈራረምና ከአጋር ድርጅቶች የሚገኘውን ሀብት ውጤታማና በተቀላጠፈ አኳኋን ማስተዳደርና አፈጻጸሙን መከታተል፣ እንዲሁም ክፍላተ ኢኮኖሚ ጋር ያለዉ ትስስር መገምገም፣ የልዩ ወረዳውን መንግስት የፋይናንስና ንብረት ኢንስፔክሽን ማከናወን፣ እርምጃ መውሰድና እንድወሰድ ማድረግ፣ ዘመናዊ የበጀት አስተዳደር፤ የሂሳብ አያያዝ፣ የግዥና የንብረት አስተዳደር፣ በኢኮኖሚና ማህበራዊ ልማት ዘርፍ የተሰማሩ መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ከሚመለከታቸው ጋር በመሆን ማስተባበርና መቆጣጠር፤ ለሲቪል ማኀበረሰብ ድርጅቶች የቅድመ ስምሪት የስራ ውል ፈቃድ መስጠት፣ ፕሮጀክቶችን የማበልጸግ፣ የማጽደቅና የመፈራረም ሂደትን የመምራትና የማስተባበር፤ አተገባበራቸውንም በመስክ የመከታታልና የመገምገም እንዲሁም የሀብት ፍሰትና ስርጭት ፍትሃዊነት እንዲረጋገጥ ማስቻል፣ የመንግስትና የግል አጋርነት እንዲጎልብት አሰራር ሥርዓት መዘርጋት፣ የመንግሥት ሀብትና ዕዳን የማስተዳደር እና በበላይነት የመምራት ዋና ኃላፊነት አለበት፡፡

ንግድና ገብያ ልማት ጽ/ቤት

ፍትሃዊ የንግድ አሰራርና ዘመናዊ የግብይት ስርዓትን በመዘርጋትና መልካምአስተዳደርን በማስፈን የንግዱ ማህበረሰብ ናሸማቹን ህብረተሰብ ተጠቃሚነት በማረጋገጥ እርካታ ደረጃቸውን ማሳደግ ነው

ትራስፖርትና መንገድ ልማት ጽ/ቤት

የተለያዩ ደረጃ ያላቸው መንገዶችን በማጥናት፣ በመገንባትና በመጠገን፤ በትራንስፖርት ዘርፍ አቅም በማሳደግ የባለድርሻ አካላትን በማስተባበርና በመደገፍ የትራንስፖርትና መንገድ ልማት ፖሊሲዎችና ስትራቴጂዎችን በሥራ ላይ በማዋል ቀልጣፋ፣ኢኮኖሚያዊ፣ ደህንነቱና ምቾቱ የተጠበቀና ከዞኖች ጋር የተሳሰረ የመንገድ አውታርና ዘመናዊ ትራንስፖርት አገልግሎት ስርዓት በመዘርጋት የህብረተሰቡን ፍላጎት ማሟላትና ዘርፉ ለክልሉ ዕድገት የሚጠበቅበትን ሚና እንዲያበረክት ማድረግ

ስራ እድል ፈጠራና ኢንተርፕራይዞች ጽ/ቤት

በገጠርና በከተሞች ዘላቂ የሥራ ዕድል ፈጠራ የድጋፍ ማዕቀፎችን በማጠናከርና ለኢንተርፕራይዞች መስፋፋት ምቹ ከባቢ ሁኔታ በመፍጠር የዘርፉን የቴክኖሎጂ አቅም ማሳደግ እና የሥራና ገበያ ተጠቃሚነትን ከፍ በማድረግ ሁለንተናዊ ብልጽግናን ማረጋገጥ ነው፡፡

ግብርና ጽ/ቤት

የቀቤና ልዩ ወረዳ በመሆኑም ግብርናና ገጠርን ማዕከል ያደረገውን የገጠር ልማት ፖሊሲና ስትራቴጂን በመተግበር ፈጣንና ቀጣይነት ያለው የኢኮኖሚ ዕድገት ለማስመዝገብ የልዩ ወረዳዉ ፅ/ቤት በሥሩ የተለያዩ የሥራ ሂደቶችን በማቀፍ በአዲስ መልክ ከተቋቋመ ጊዜ ጀምሮ ጽ/ቤቱ የተጣለበትን ኃላፊነት በይበልጥ ለመወጣትና ቀጥተኛ ተገልጋይ የሆነውን የአርሶ አደር ፍላጐት ለማርካት እንዲያስችለው በመሠረታዊ የአሠራር ሂደት ለውጥ ወደ ሙሉ ትግበራ በመግባት ተግባራዊ እንቅስቃሴ በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡

ህብረት ስራ ጽ/ቤት

ብቁና ተወዳደር የሆኑ ኀ/ሥራ ማህበራትን በማዳራጀትና በማስፋፋት ፋይናንስ ሥርዓት በማሻሻለ ረገድ ድርሻቸዉን በማሰደግ ዘመናዊ የግብይት ሥረዓት በመዘረጋት የህብረተሰቡን ገቢ በማሰደግ ለወረደችን ብሎም ለሀገር ኢኮኖሚ ዕድገት የላቃ ድርሻ መበርከት

ደን አካባቢ ጥበቃና ልማት ጽ/ቤት

በአየር ንብረት ለዉጥ ምክንያት የሚደርሰዉን የድርቅ አደጋ በአስተማማኝ ደረጃ ለማቋቋም የደን ሀብቱን ተንከባክቦ የተፈጥሮ ስርዓተ-ምህዳሩ ሚዛን ሳይዛባ ለትዉልድ ለማቆየት .፣ ፈጣንና ቀጣይነት ያለዉን የኢኮኖሚ እድገት ለማረጋገጥ ልዩ ትኩረት የሚሹ ተግባራትን በመለየት ከባለ ድርሻ አካላት ጋር ሊኖር የሚገባዉን ትስስርና ቅንጅት ለማጠናከርም እየተሰራ ይገኛ ልየልዩ ወረዳችን የደንሽፋን እና የብዝሀ-ሕይወት የልዩ ወረዳዉን የደንሽፋን የማሳደግ፣ከአፈርብክለት የመጠበቅ እንዲሁም በልዩ በወረዳዉ የሚከናወኑ ማንኛውም እንቨስትመንት በአካባቢ እና ማህበረሰብ ላይ የጎላተፅዕኖ እንዳያደርስ፣በልዩ ወረዳዉየብዝሀ-ሕይወትሀብት መመናመንን በማስቀረት የተጎዳ ስርዓተ-ምህዳርን መልሶ በማልማት ማህበረሰቡን ከስርዓተ-ምህዳር ግልጋሎት ተጠቃሚ በማድረግ በምቹ እና በፅዱ አከባቢ የመኖር ዋስትና ማረጋገጥ ነው

ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ጽ/ቤት

በልዩ ወረዳ ተወዳደሪና ብቁ የሆነ የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ በመፍጠር፣በከተሞች የአካባቢ ልማትን በማፋጠን፣የከተማ-ከተማና የከተማ-ገጠር ትስስርን በማጠናከር ለከተማ ልማት ምቹ ሁኔታ በመፍጠር ከተሜነትን ማሳደግና ዘላቂ የሆነ ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና አካባቢያዊ ልማት ማረጋገጥ ነው፡፡

ኢንቨስትመንትና ኢንዳስትሪ ልማት ጽ/ቤት

የልዩ ወረዳችን የኢንቨስትመንት አማራጮች በማጥናት፣በማስተዋወቅ፣የኢንቨስትመንት ፈቃድና መሬት በመስጠት ልማታዊ ባለሀብቶችን በማበረታታት እንዲሁም የኢንቨስትመንት አፈጻጸማቸውን በመከታተልና የሚከሰቱ ችግሮች የሚፈቱበትን አሰራር በመቀየስ በልዩ ወረዳዉ የግል ኢንቨስትመንትን ማስፋፋትና ማጠናከር ነው፡፡

ፕላን ልማት ጽ/ቤት

ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች በሚመለከት ሀሳቦችን በማመንጨት፣ ግልፀኝነትና ተጠያቂነት በሰፈነበት አሰራር ዘመናዊ የልማት ዕቅድና መረጃ በመዘርጋት፣የልማት አጋሮችን በማስተባበርና የሕዝብ ቁጥር ዕድገት ከኢኮኖሚ እድገት ጋር እንዲጣጣም በመስራት በልዩ ወረዳዉ ፈጣንና ቀጣይነት ያለው ልማት እንዲረጋገጥ ማስቻል፡፡

ውሃ ማእድንና ኢነርጂ ጽ/ቤት

ለህብረተሰቡ የሚገነቡ የመጠጥ ውሃ ተቋማት አስተማማኝና ዘላቂ አገልግሎት መስጠት እንዲችሉ በዕቅድ ዘመኑ ለመጠጥ ውሃ ተቋማት ጥናትና ዲዛይን ስራ ከፍተኛ ትኩረት ተሰጥቶ የሚሰራ ሲሆን በውሃ ሀብት ጥናትና አስተዳደር ረገድም ለሕብረተሰቡ ለመጠጥ የሚቀርበው ውሃ የጥራት ደረጃው የተረጋገጠ እንዲሆን፣ ሚዛናዊና ፍትሃዊ የውሃ ሀብት አጠቃቀም እንዲሰፍን፣ የውሃ ሀብት አጠቃቀም በህጋዊ ፈቃድ ላይ የተመሰረተ እንዲሆን እና በውሃ አካላት ላይ ብክነትና ብክለት እንዳይደርስ አስፈላጊው ወቅታዊ ክትትልና ቁጥጥር ማድረግ የሚያስችል ስራ የሚከናወን ይሆናል፡፡ ከሁሉም በላይ የህብረተሰቡን አቅም በሚገባ አሟጦ መጠቀም በተለያየ የመንግስት ፕሮግራም በተፈቀደ በጀት የሚገነቡ ግንባታዎች የጨረታና የኮንትራት አስተዳደር ውስንነቶች በማስወገድ በተያዘለት ጊዜ በጥራት ከማንኛውም የኪራይ አመለካከት እና ተግባር በፀዳ መልኩ እንዲተገበርና ሁሉም የገጠር መጠጥ ውሀ ተቋማት ህጋዊ ሰውነት ባለው አደረጃጀት እንዲተዳደሩ ለማድረግ ጥረት ይደረጋል።

የኢኮኖሚ ዘርፍ አገልግሎቶች

ለበለጠ መረጃ እና አገልግሎቶች እኛን ያግኙን

አግኙን

የኢኮኖሚ ዘርፍ ዜናዎች

ኢኮኖሚ

''በራስ አቅም ለመቆም የገቢ አቅምን አሟጦ መጠቀም ይገባል'' !!!

''በራስ አቅም ለመቆም የገቢ አቅምን አሟጦ መጠቀም ይገባል'' !!!...

ተጨማሪ ያንብቡ
ኢኮኖሚ

በፀደይ እርጥበት የተዘራው የሽምብራ ሰብል በጥሩ ሁኔታ ላይ የሚገኝ መሆኑን ተገለፀ።

በፀደይ እርጥበት የተዘራው የሽምብራ ሰብል በጥሩ ሁኔታ ላይ የሚገኝ መሆኑን ተገለፀ። (ወል...

ተጨማሪ ያንብቡ
ኢኮኖሚ

የልዩ ወረዳውን የውሃ ሽፋን ለማሳደግ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን የቀቤና ልዩ ወረዳ ውሃ መስኖና ማዕድን ልማት ፅ/ቤት ገለፀ፡፡

የልዩ ወረዳውን የውሃ ሽፋን ለማሳደግ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን በማዕከላዊ ኢትዮጲያ ክል�...

ተጨማሪ ያንብቡ
ኢኮኖሚ

የቀቤና ልዩ ወረዳ ግብርና ጽ/ቤት " የተቀናጀ ግብርና ልማት ጥረት ለሀገራዊ ማንሰራራት" በሚል መሪ ቃል የ2017 በጀት ዓመት የማጠቃለያ ጉባኤና የ2018 የበጋ ወቅት ስራዎች የንቅናቄ መድረክ አካሄደ።

የቀቤና ልዩ ወረዳ ግብርና ጽ/ቤት " የተቀናጀ ግብርና ልማት ጥረት ለሀገራዊ ማንሰራራት" በሚል...

ተጨማሪ ያንብቡ
ኢኮኖሚ

የቀቤና ልዩ ወረዳ ገቢዎች ጽ/ቤት በአዲሱ የገቢ ግብር አዋጅ ቁጥር 1395/2017 ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ መድርክ በወልቂጤ ከተማ አካሄደ።

የቀቤና ልዩ ወረዳ ገቢዎች ጽ/ቤት በአዲሱ የገቢ ግብር አዋጅ ቁጥር 1395/2017 ዙሪያ የግንዛቤ ማስ�...

ተጨማሪ ያንብቡ