አስተዳደርና ህግ ዘርፍ
የቀበና ልዩ ወረዳ አስተዳደርና ህግ ዘርፍ የተለያዩ አስተዳደራዊ እና ህጋዊ አገልግሎቶችን ለህዝብ በማቅረብ ላይ ይገኛል።
አስተዳደር ጽ/ቤት
በልዩ ወረዳው ያሉትን ሰብዓዊና ተፈጥሮዓዊ ሀብቶች አቀናጅቶ በመምራት ቀጣይነት ባለው መልኩ በስፋት ጥቅም ላይ ለማዋልና የብሄረሰቦች አንድነት በማጠናከር ማህበራዊ ኢኮኖሚያዊ ልማትን በማፋጠን መልካም አስተዳደርና ዲሞክራሲያዊ ስርዓት ግንባታ እንዲጎለብት ማድረግ፡፡
ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ጽ/ቤት
በልዩ ወረዳው የመንግስትን ፖሊሲዎችና ስትራቴጀዎች በብቃት ለመፈጸም የሚያስችሉ አዳዲስ አሰራሮችንና አደረጃጀቶችን በመዘርጋት፣የአመራሩንና የሰራተኛዉን አመለካከት በመለወጥና ብቃቱን በማሳደግ፣ህዝብን በቅንነትና በታማኝነት የሚያገለግል ጠንካራና ዉጤታማ የመንግሥት አገልግሎት መፍጠር ነው፡፡
ፍትህ ጽ/ቤት
በልዩ ወረዳው መልካም አስተዳደርን ማሳደግ እንዲቻል፣ የሚከሰቱ የወንጀል ጉዳዮችን በማጣራት፣ ክስ በማቅረብና በመከራከር፣ እንዲሁም በልዩ ወረዳ መንግሥት የሚከሰሱባቸውን የፍትሐብሔር ጉዳዮችን በመከታተል፣ የመንግሥትና የሕዝብ ጥቅም ማስጠበቅ፣ ፍትሕን ተደራሽ ማድረግ፣ እንዲሁም በተፈረደባቸው ወንጀል በህግ ጥላ ስር በማረፉያና በማረሚያ ቤቶች የሚገኙ ዜጎች ሰብዓዊ መብታቸው እንዲጠበቅ ተገቢውን ክትትል በመፈጸም፣ አያያዝ በህግ አግባብ እንዲሆን ማረጋገጥና አምራች ዜጎች እንዲሆኑ ማድረግ ነው።
ከፍተኛ ፍርድ ቤት
ፍ/ቤቶች የመልካም አስተዳደር መስፈን፣ ለዲሞክራሲ ስርዓት ግንባታ፣ ለልማት መፍጠን፣ ለምቹ ኢንቨስትመንት እንዲሁም ለሀገራዊ ሰላምና ደህንነት ያላቸው ድርሻ እጅጉን የጐላ ነው፡፡ይህን ውጤት ለማምጣት በስትራቴጂ፤ በህግና በዕቅድ የሚመሩ መሆን እንዳለባቸው የማይካድ ሀቅ ነው፡፡ በመሆኑም ፍ/ቤቶቻችን የህብረተሰባችንና የመንግስት የፍትህ ፍላጐት ታሳቢ በማድረግና ህዝቡ ያገኘውን ህገ-መንግስታዊ መብት እንደምቹ አጋጣሚ በመጠቀም ፈጣን፤ ፍትሀዊ፤ ወጪ ቆጣቢና ተገማቺነት ያለው በመላው ህብረተሰብና መንግስት በነፃነትና በገለልተኝነት ዳኝነት/ፍትህ/ የሚሰጥበት ተቋም እንደሆነና በሚሰጣቸው ውሳኔዎችም መሉ እምነት የሚጣልበት አንዱና ዋነኛው የመንግስት ምሰሶ እንዲሆን ከፍተኛ ጥረት ይደረጋል፡፡
የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት
የቀቤና ልዩ ወረዳ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በወረዳው ውስጥ ያሉ የቤተሰብ፣ የንብረት፣ የመሬት፣ የስራ ግንኙነትና ቀላል የወንጀል ጉዳዮችን በመጀመሪያ ደረጃ የሚመርምርና ውሳኔ የሚሰጥባቸው የአካባቢ ፍርድ ቤት ነው።
ፖሊስ ጽ/ቤት
የቀቤና ልዩ ወረዳ ፖሊስ ጽ/ቤት ይህንን የተመዘገበውን አበረታች ውጤቶች አስተማማኝ በማድረግ የልዩ ወረዳችን ህ/ሰብ ሰላምና ፀጥታ በአስተማማኝ ሁኔታ በማረጋገጥ የህግ የበላይነትና የዜጎችን ሰብአዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶችን በማክበርና በማስከበር እንዲሁም የቀበሌ ፖሊስ አገልግሎት መስጫን ድጋፍና ክትትል በማድረግ የልዩ ወረዳው ህ/ሰብ ያሳተፈ የወ/ል መከላከል ተግባር ተደራሽ በማድረግ የማህበረሰብ አቀፍ ስራዎችን በመስራትና የተለያዩ ወ/ል የፈፀሙ ተጠርጣሪዎችን ለህግ በማቅረብ ምርመራውን በማጣራት ፈጣንና ቀልጣፋ አገልግሎት በመስጠት የልዩ ወረዳችን ሰላምና ፀጥታ አስተማማኝ ማድረግ ነው፡፡
ሰላምና ፀጥታ ጽ/ቤት
የዜጎች ሰብአዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶች፣የወሳኝ ኩነቶች መረጃ የህግ የበላይነትና መልካም አስተዳደር፣የህዝቡ ሠላም፣ ፀጥታና ደህንነት የተረጋገጠበት ልዩ ወረዳ ተፈጥሮ እና ለዚህም የበኩሉን ጉልህ ድርሻ የሚያበረክት ተቋም ሆኖ ማየት
የህዝብ ተወካዮች ምክርቤት
ም/ቤቶች በህዝብ ውክልና የተመሰረቱ ተቋማት በመሆናቸው የህዝብ ሉአላዊነት የዲሞክራሲ ስርዓት መገለጫዎች የኢኮኖሚያዊ ማህበራዊና በፖሊቲካ ጉዳዮች ላይ የህዝብ ተሳትፎ የሚረጋገጥባቸው ማዕከላት ናቸው፡፡ በተጨማሪም በተለያየ ደረጃ የሚገኝ ህ/ሰብ ከልማት እና መልካም አስተዳደር ተጠቃሚ ለማድረግ የመንግስት ተቋማት የተቋቋሙበት አላማና የሚሰጡት አገልግሎት በህግ በመደንገግ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ አገልግሎቶች ተደራሽ እንዲደረግ ይወስናሉ ፤በመንግስት ተቋማት በጀትና ዕቅድ በማጽደቅ ስራ ላይ እንዲውል ያደርጋሉ፡፡
ሚሊሻ ጽ/ቤት
በቀቤና ልዩ ወረዳ በህብረተሰቡ ንቁ ተሳትፎ ብቃት ያለው የሚሊሻ ኃይል በመመልመል፣በማሰልጠን፣በማደራጀት፣ በማሰማራት፣በማጥራትና የሎጅስቲክስ አስተዳደር ጉዳዮችን በማስፈፀም፤የሚሊሻ ኃይል ማደራጀትና የአገልግሎት አሰጣጥ ተደራሽነት በማረጋገጥ የአካባቢ ፀጥታ ማስከበርና የህብረተሰቡን ሠላምና ደህንነት መጠበቅ