በልዩ ወረዳው በፍርድቤትና በፍትህ ዘርፉ በ2018 1ኛሩብ አመት የተሻለ አፈፃፀም መመዝገቡ ተገለፀ።
21 Oct 2025

ይህ የተገለፀው የልዩ ወረዳው ከፍተኛ ፍርድቤት፣ፍትህ ፅ/ቤት እና ፖሊስ ፅ/ቤት በ2018 በጀት አመት የ1ኛ ሩብ አመት የእቅድ አፈፃፀም የጋራ የግምገማ መድረክ ባካሄዱበት ወቅት ነው።
(ወልቂጤ፣ጥቅምት 11/2018 ዓ/ም)
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የቀቤና ልዩ ወረዳ ከፍተኛ ፍርድ ቤት፣ፍትህ ፅ/ቤትና ፖሊስ ፅ/ቤት በጋራ በመሆን በ2018በጀት አመት የ1ኛ ሩብ አመት የእቅድ አፈፃፀም የግምገማ መድረክ ተጠሪ ተቋማትና ከባለድርሻ አካለት በተገኙበት አካሂደዋል ።
በመድረኩም በ2018 በጀት አመት የ1ኛ ሩብ አመት የእቅድ አፈፃፀም ሪፖርት በሶስቱም ተጠሪ ተቋማቱ አቅርበው ውይይት ተደርጎባቸዋል።
የቀቤና ልዩ ወረዳ ከፍተኛ ፍርድቤት ፕሬዝዳንት የተከበሩ ሙከረም ኑረዲን እደተናገሩት ፍርድ ቤቶች የአገልግሎት አሰጣጣቸውን በማሻሻል ተደራሽ መሆን እንደሚጠበቅባቸው ገልፀው ከባለድርሻ አካላት ጋር መሰል መድረኮችን መፍጠር ለቀጣይ የተግባር አፈፃፀም አጋዥ መሆኑን ተናግረዋል።
ፕሬዝዳንቱ አክለውም የህግ የበላይነት በማስፍን ዜጎች በነፃነት ውጥተው የሚገቡበት የተሻለ ልዩ ወረዳ ለመፍጠር በቅንጅት እንደሚሰራም ተናግረዋል።
በተመሳሳይ በመድረኩ የተገኙት የቀቤና ልዩ ወረዳ ምክትል አስተዳዳሪና የፍትህ ፅ/ቤት ሀላፊ አቶ አብድልማሊክ አብደላ እንደተናገሩት የህዝብን ፍትሐዊ ተጠቃሚነት በሚያረጋግጥ መልኩ በፍትህ፣ በሰላምና በፀጥታ፣ በመደበኛ ወንጀሎችና በሌሎችም ጉዳዮች ላይ ከሚመለከታቸው አካላትና ተጠሪ ተቋማት ጋር ተቀናጅተው በመስራታቸው የተሻለ ውጤት መምጣት ችሏል ብለዋል።
አክለውም በቀጣይም በዘርፉ የሚሰሩ ስራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ በመግለፅ የልዩ ወረዳው ህዝብ የፍትህ ተጠቃሚነቱን ለማረጋገጥ ቅንጅታዊ አሰራሩን አጠናክረው እንደሚያስቀጥሉ ገልጸዋል።
የቀቤና ልዩ ወረዳ ፖሊስ ፅ/ቤት ኃላፊ ም/ኢንስፔክተር ፈድሉ ሳኒ እንደተናገሩት ከዚህ በፊት መሰል መድረኮች ተፈጠረው በተደረጉ ውይይቶችና ቅንጅታዊ ስራዎች ውጤቶች ማምጣት መቻሉ ተናግረው በመድረኮቹ ጉድለቶችን ለማረምና ተግባራትን ለማሻሻ ወሳኝ በመሆኑ ማስቀጠል እንደሚገባም አሳስበዋል።
ምክትል ኢንስፔክተሩ አክለውም ወንጀል ነክ ጉዳዮች በልዩ ወረዳው እንዳይፈፀሙ ለመከላከል እና ከተፈፀሙ በኋላ ወንጀለኞችን ለፍርድ ለማቅርብ ከሚመለከተው አካላት ጋር በመቀናጀት እንደሚሰሩ ተናግረዋል።
በመድረኩም በቀረቡት ሰነዶች መነሻነት ከተሳታፊዎች ሀሳብ አስተያየት የተነሱ ሲሆን በተነሱት ሀሳቦች እና አስተያየቶች ሰፋ ያለ ውይይት ተደርጎባቸው ምላሽ ማብራሪያ የሶስቱም ተጠሪ ተቋማት ሀላፊዎች እና የማኔጅመንት አካላት ምላሽ እና ማብራሪያ ሰጥተዋል።
በተጨማሪም ጥንካሬዎችን ማስቀጠልና በጉድለት የተለዩትን በቀጣይ በማሻሻል የቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎችም ተመላክተዋል።
በመጨረሻም ተቋማቱን በዳኝነትና ፍትህ ዘርፍ የተቋማት ጥምርታ የአሰራር ስርአት በመወሰኛ የእስትራቴጂክና የማንዋል ስምምነት ተፈራርመው መድረኩ ተጠናቋል ።
********************
በሙከረም አለዊ
********************
#ውጤታማ የመረጃ ልውውጥ ለልማት !!
****************************
ፈጣንና ትኩስ መረጃዎችን በሌሎች የሚዲያ አማራጮች ይጠቀሙ‼️
👉Facebook https://www.facebook.com/profile.php?id=100072292788562&mibextid=ZbWKwL
👉Instagram https://www.instagram.com/qebenacomm?igsh=NHRiZjFybHk4dmRn
👉Twitter https://x.com/KebenaO88374?t=T_ncptfwuNAwRnhxrqdM9w&s=09
👉Telegram channel
https://t.me/Qebena1
👉youtube
https://youtube.com/@kebenaspecialworedacomm?si=DOrrIJYDBKMzjXCr
👉tiktok
tiktok.com/@kebenacommuni

ተጨማሪ ምስሎች