ሚዲያ በደረስንበት የቴክኖሎጂ ዘመን አጥፊም አልሚም መሆን እንደሚችል ተመልክተናል ። በተለይ ሚዲያን ለልማት በማዋል ከፍተኛ ሀገራዊ ጥቅም ያካባቱ ሀገራት ቁጥራቸው የትየለሌ ነው። በዛው ልክ ደግሞ ሚዲያን ላልተገባ አላማ፣ ህዝብን ከህዝብ ለመለያየት፣ ለጥላቻ ንግግር የሚጠቀሙ ባለባቸው ሀገራት በችግር ላይ ችግር እየደራረቡ ልማት ናፋቂ ከመሆን አልፈው እንደሀገር የመፍረስ አደጋ የተጋረጠባቸው ሀገራትም ሞልተዋል ።
We have seen that media can be both destructive and beneficial in the technological age we have reached. There are many countries that have achieved great national benefits by using media for development. At the same time, there are also many countries that use media for unwarranted purposes, to divide people from others, and to spread hate speech, piling up problems on top of problems, not only hindering development, but also facing the risk of collapse as a country.
ያለንበት የዲጂታል አለም በየእለቱ በርካታ ኩነቶችን የምታስተናግድበትን ሁኔታ ሚዲያው በየማይክሮ ሰከንዱ ወደ አድማጭ ተመልካች እያደረሰ አለም አንድ መንደር መሆኗን በተጨባጭ እያሳየ በሚገኝበት በዚህ ዘመን ሚዲያ የማይተካ ሚና ሲጫወት ይታያል ።
In this era of digital world, where the media is delivering a multitude of events every day to the audience every microsecond, demonstrating that the world is a global village, the media is playing an irreplaceable role.
እንደ ሀገራችን የሚዲያ እንቅስቃሴም በተመሳሳይ በመንግስት የሚከናወኑ የልማት እንቅስቃሴዎች እና በየእለቱ የሚከሰቱ ኩነቶችን በመከታተል ለህዝብ የሚያደርሰው ሚዲያ በሀገራችን ፖለቲካዊ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ዘርፍ ትልቅ አወንታዊም አሉታዊ ተፅእኖ በመፍጠር ላይ ይገኛል ።
የቀቤና ልዩ ወረዳ የሚዲያ እንቅስቃሴ ገና ዳዴ እያለ ያለ ቢሆንም በልዩ ወረዳው የሚሰሩ የመንግስት እና የፓርቲ ስራዎች ህዝብ እንዲያውቃቸው ከማድረግ በተጨማሪም ህዝብና መንግስትን ለማገናኘት እንደ አይነተኛ መሳሪያ ያገለግላል።
As with the media movement in our country, there is also a huge positive and negative impact on the political economic and social sector of our country by monitoring the development activities and daily events of the government.
While the media activity of the Kabe and special district is still Dade, it also serves as a typical tool to connect the people and the government with the people working in the special district.
የቀቤና ልዩ ወረዳ የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ፅ/ቤት በልዩ ወረዳው የሚከናወኑ የልማት ፣የመልካም አስተዳደር ጉዳዮችን ለይቶ አፈፃፀማቸውን እግር በእግር እየተከታተለ በተለያዩ የሚዲያ አማራጮች ለህዝብ እንዲደርሱ ያደርጋል። በተጨማሪም የባህል፣ቋንቋ፣ታሪክ ፣እሴቱ የቱሪዝም መዳረሻዎችን በማስተዋወቅ ልዩ ወረዳው ለልማት ያለውን ከፍተኛ አቅም ለሌላው አለም ለማስተዋወቅ ይሰራል ።
The kebena and special district government communications office identifies development, good governance issues in the special district and monitors their performance foot-by-foot and makes them accessible to the public through a variety of media options. In addition, its cultural, linguistic, historical, value works to promote tourism destinations to the rest of the world through the high potential of the special district for development.